+251 96 011 8811     info@hohitetibeb.edu.et
US English
ET አማርኛ

እንኳን ወደ ኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት በደህና መጡ

ተጨማሪ ይፈልጉ

በትምህርት የላቀ አገልግሎት

ተጨማሪ ይፈልጉ

ንቁ የተማሪዎች ሕይወት

ተጨማሪ ይፈልጉ

ትምህርት ለተሻለ መጻኢ ዕድል

በኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ሙሉ አቅማቸውን እንዲያወጡና ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎች እንዲሆኑ የሚያስችል፣ አሳታፊና አነቃቂ የመማር ማስተማር ስልትን በመተግበር እንዲሁም ምቹ የመማሪያ አካባቢን በመፍጠር ለተሻለ ውጤት እንሠራለን።

ስለ ኆኅተ ጥበብ

ኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት "በጳዝዮን አክስዮን ማኅበር" አማካኝነት በ2018 ዐ.ም የተመሠረተ ሲሆን የትምህርት አሰጣጥ ብቃትን ከሥነ ምግባር ጋር በማቀናጀት የትምህርት አገልግሎት ለመስጠት ተመሠረተ።

ተቋማችን አገር በቀል እውቀቶችንና ባሕላዊ እሴቶችን ባከበረ መልኩ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሥርዓተ ትምህርትን ይሰጣል። በሥነ ምግባር የደረጀ ትውልድ ለመተካት ቁርጠኛ የሆኑ መምህራኖቻችንም የእያንዳንዱን ተማሪ ልዩ ተሰጥዖ ለማሳደግ በትጋት ይሠራሉ።

በዘመናዊ የማስተማሪያ ግብዐቶች፤ ተማሪ ተኮር የማስተማር ሥነ ዘዴን በመጠቀም ተማሪዎቻችንን ለከፍተኛ ትምህርት እና ለቀጣይ ስኬታማ ሕይወት እንዲኖራቸው እናዘጋጃቸዋለን።

በተጨማሪም ሥነ ምግባር ያለውና በራስ የመተማመን መንፈስ የተላበሰ ዜጋ ለመገንባት ከመደበኛው ትምህርት ጎን ለጎን መሠረታዊ የግብረ ገብና የልሳነ ግእዝ ትምህርትን እንሰጣለን።

ተጨማሪ ይፈልጉ

ርዕይ

አገራቸውን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ለማሳደግ የሚተጉ፤ በሥነ ምግባር የበለጸገ ትውልድ በማፍራት በዘርፉ ከተሠማሩ ትምህርት ቤቶች ቀዳሚ ተመራጭ ሆኖ ማየት።

ተልዕኮ

አገር በቀል እውቀት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን፣ አስፈላጊ የትምህርት ግብዓትን በማሟላት በሥነ ምግባር የታነጹ፣ በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት የበቁ ተወዳዳሪ ትውልድ ማፍራት።

እሴቶች

ቅንነት, አክባሪነት, ተመራጭ, ጥራት, ፈጠራ, ተጠያቂነት ተባባሪነት, ተሰጥዖን ማጎልበት, ኅበረሰብን ማገልገል

የትምህርት ዘርፎች

ቅድመ አንደኛ ት/ቤት (መዋዕለ ሕፃናት)

የቅድመ አንደኛ የትምህርት መርሐ ግብራችን ትኩረት የሚያደርገው ተማሪዎቻችን ሳቢና አዝናኝ በሆነ አቀራረብ ንባብና ጽሕፈትን፤ ቁጥሮችንና መጠኖችን እንዲያውቁና እንዲለዩ በማስተማር ከጓደኞቻቸው ጋር የመተባበርና የመግባባት ክህሎትን እንዲዳብሩ አካባቢያቸውንም እንዲገነዘቡ ማስቻል ነው።


ተጨማሪ ያንቡ

አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

ይህ ወቅት ተማሪዎቻችን ለሁለተኛ ደረጃና ከዚያ በላይ ለሆኑ ትምህርቶች አስተማማኝ ድልድይ የሚገነቡበት ወቅት እንደመሆኑ የፈጠራ አድማሳቸውን ለማሳደግ በጥያቄና መልስ፣ በንባብ ራሳቸውን እንዲረዱ በማለማመድና በማነቃቃት...የቋንቋና የሂሳብ ብቃትን፣ አካባቢያቸውንና ተፈጥሮን እንዲገነዘቡ፣ ሳይንስን እንዲረዱና የፈጠራ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ፣ እንዲሁም የመልካም ሥነ-ምግባርና የአካላዊ ብርታትን እሴቶች በአንድ ላይ በማቀናጀት፤ ተማሪዎች ለወደፊት የትምህርት ሕይወታቸውና ለተሟላ ሰብእና የሚያስፈልጋቸውን ቁልፍ መሣሪያዎች በታላቅ ጥበብ የምናስታጥቅበት የእውቀት ማዕከል ነው።

ተጨማሪ ያንቡ

መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

የመካከለኛ ደረጃ የትምህርት መርሐ ግብራችን ትኩረት የሚያደርገው በተፈጥሮ ሳይንስና ማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች ጥልቅ እውቀት እንዲኖራቸው፣ ቴክኖሎጂን ለትምህርት ዓላማ የመጠቀም አቅማቸውን በመገንባት፤ በራስ መተማመናቸው የጎለበተ፣ ራሳቸውን ለተሻለ ነገ የሚያዘጋጁ ሥነ ምግባር የተላበሱ ሆነው ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የምናዘጋጅበት ወቅት ነው።


ተጨማሪ ያንቡ

የምዝገባ ገጽ

የምዝገባ መስፈርቶች

ዕድሜ፣ የልደት ካርድ፣ የትምህርት ማስረጃ፣ ከሌላ ትምህርት ቤት ከሆነ መልቀቂያና መሸኛ ደብዳቤ፣ የተቋሙን እሴቶች ማክበርና መተግበር...

የምዝገባ ቀነ-ገደቦች

የማመልከቻ ጊዜ : ነሐሴ ፡ 2018 ዓ.ም

ነጻ የትምህርት ዕድል

ከፍለው መማር ለማይችሉ የተሻለ የትምህርት አቅም ላላቸው ተማሪዎች እንዲሁም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች በሽልማት መልክ የነጻ የትምህርት ዕድሎችን የምናመቻች ሲሆን በተጨማሪም ማኅበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት የነጻ የትምህርት ዕድሎችን ድጋፍ ለሚያሻቸው አካላት አቅም በፈቀደ መጠን እናመቻቻለን።

አስፈላጊ መረጃዎች

ተማሪዎቻችን

ልዩ ልዩ ዝግጅቶች

መንፈሳዊና ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚያዳብሩ እንዲሁም ለልጆች መነቃቃትንና ደስታን የሚሰጡ የተለያዩ በዓላትንና ዝግጅቶችን እናከናውናለን።

የንባብ ቀን

ፊደላትን እንዲለዩ ትርጉማቸውን እንዲገነዘቡ እንዲሁም የንባብ ልምዳቸውን እንዲያዳብሩ የንባብ ቀንን በልዩ ሁኔታ ለተማሪዎቻችን እናዘጋጃለን።

የእውቀት ሽግግር ቀን

መምህራንና ከወላጆች እንዲሁም ከተጋባዥ እንግዶች ልዩ ልዩ እውቀቶችን እንዲቀስሙ፤ እርስ በርስ ያወቁቱን እውቀት እንዲጋሩ፣ የአገራቸውን ታሪክ፣ ወግና ሥርዓት እንዲገነዘቡ ይደረጋል።

ማኅበረሰባዊ አገልግሎት

በትምህርት ቤት ለትምህርት ማኅበረሰቡና በአካባቢው ለሚገኙ የአካባቢው ማኅበረሰብ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግና አካባቢን ንጹሕና ማራኪ የማድረግ ተግባራትን መከወን።

ሥራ አስፈጻሚዎች

ጥራት ያለው ትምህርትን ለማቅረብ በመትጋት ላይ ያሉ የኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት አመራሮች።

ተገኝወርቅ ታደሰ

ሥራ አስኪያጅ

በአስተዳደር ዘርፉ ላይ የ8 ዓመት ልምድን በማካበት ዘርፉን ለማጎልበት ተቋሙን ከማደራጀት ጀምሮ በሥራ ላይ ይገኛሉ።

ሙሉወርቅ አድማሱ

ርዕሰ መምህር

በትምህርት ዘርፉ በአጠቃላይ 16 አመት ያገለገሉ ሲሆን በዳይሬክተርነት የ15 ዓመት ልምድን አካብተዋል።

ዲ/ን ወረቀት ግዛቸው

ርዕሰ መምህር

በትምህርት ዘርፉ በአጠቃላይ 16 አመት ያገለገሉ ሲሆን በዳይሬክተርነት የ10 ዓመት ልምድን አካብተዋል።

አስተያየትና ምስክርነቶች

ስለ ኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት ተሞክሮ እና ልምድ ከማህበረሰባችን የተሰጡ አስተያየቶች።

Parent

አቶ ምትኬነህ አለማየሁ

የተማሪ ቤተሰብ

"የኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት ልጆቼን በልዩ የትምህርት አሰጣጥ እንዲያልፉና እና መምህራኑ ቁርጠኛ በመሆን እያበቁ ነው። የትምህርት መገልገያዎቹም እጅግ በጣም ጥሩ እና ተደራሽ ከመሆናቸውም ባሻገር የብዝሃ-ባህላዊ አከባበሩ ልጆቼን በሚገባ ሀገራቸውን እንዲያውቁና የተካነ ስነ-ልቦና እንዲኖራቸው ረድቷቸዋል።"

Student

ቶሎሳ አበበ

መምህር

"የኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት የመማር እና የማስተማር ልምምዶች ከፍተኛ ትኩረት የሚስቡ እና ተማሪዎችን ያማከሉ ሲሆኑ፣ በፈጠራ እና በተግባራዊ ክህሎት ልማት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣሉ። እኛ መምህራንም ቁርጠኝነትን እና ሙያዊነትን በተላበሰ መልኩ ለተማሪዎቻችን ባላቸው የትምህርት ደረጃ ማወቅ ያለባቸውን ነገር አውቀው እንዲያልፍ እና ክህሎታቸውን እንዲያጎለብቱ እንድናበቃቸው እንበረታታለን።"

Student

ታምሩ አግንቸው

የአካባቢው ወጣት

"በኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት የሚገኙ አስተማሪዎች ውስብስብ ፅንሰ ሀሳቦችን እንዲረዱና ማኅበረሰባዊ ሰነ-ልቦና እንዲኖራቸው ለማድረግ ከምንም በላይ ጥረት ያደርጋሉ። ለራዕያቸው ያላቸው ቁርጠኝነትና ትጋት በእውነት አነቃቂ ነው።"

Student

አቶ ካሳሁን ሰቦቃ

የተማሪ ወላጅ

"የት/ቤቱ መሠረተ ልማትና የትምህርት ግብዓቶችና ጥራት በደረጃ መሻሻላቸው አበረታች ነው። የት/ቤቱ የመማሪያ ሀብቶችን እንዲሁም ክፍሎችን ለተማሪዎች የተሻለ አካባቢ ለመፍጠር የሚደረገውን ቀጣይ ጥረት እናመሰግናለን።” እነዚህ ጥረቶች ውጤታማ ትምህርትን ይደግፋሉ እና ተማሪዎች በምቾትና በራስ-መተማመን እንዲማሩ ያግዛሉ። "

Alumni

ኢንጅነር ሲሳይ

የተማሪ ወላጅ

"ለልጃችን ትምህርትና ግል እድገት የማያቋርጥ ትጋት ለሚያደርጉ የት/ቤቱ አስተዳደርና መምህራን ከልባችን እናመሰግናለን። ልጃችን በየቀኑ በት/ቤቱ ደህንነት፣ ክብር እና የመማር መነሳሳት እያገኘ መሆኑ ያስደስተናል። በትምህርት አፈፃፀም፣ በራስ-መተማመን እና በዲሲፕሊን ግልፅ ልማት እንዳለ አይተናል። የሚሰጠው ደጋፊ የመማሪያ አካባቢ እና ከቤተሰቦች ጋር የሚደረገው መደበኛ ግንኙነት በጣም የሚያስደንቅ ነው"

ግብዓቶች

ሚያዝያ 2018 ዓ.ም

እሑድ
ሰኞ
ማክሰኞ
ረቡዕ
ሐሙስ
አርብ
ቅዳሜ

የተማሪዎች መረጃ ስርዓት

የህ የኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት የተማሪ መረጃ ስርዓት (SIS) ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለአስተማሪዎች እና ለአስተዳዳሪዎች የተማሪ መረጃ ሁሉ ከምዝገባ እና ከምዘና እስከ ክፍያ እና መርሐ-ግብር ድረስ የሚያስተዳድር ደህንነቱ የተጠበቀ ማዕከላዊ ዲጂታላዊ መድረክ ነው።


ወደ መረጃ ስርዓት ይግቡ

የዲጂታል መጽሐፍት ግብዓቶች

ይህ የኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት ተማሪዎችን እና ሠራተኞችን በትምህርት ቤቱ ያሉ ኤ-መጻሕፍት፣ የአካዳሚክ መጽሔቶች፣ ማህበረ-መረጃዎች እና ያለፉት ፈተናዎችን ባሉበት ሁነው እንዲያገኙና ተደራሽ ለማድረግ የሚያገለግል ዲጂታል ቤተመጽሐፍትን ነው።


ዲጂታል ቤተ - መጽሐፍቱን ይጎብኙ

ትምህርታዊ ግብዓቶችን እዚህ ያግኙ

ትምህርታዊ እቅዶች

ዓመታዊ የትምህርት ዕቅዶችን እና የትምህርት መርሐ-ግብሮችን እዚህ ይከታተሉ።

እቅዱን ያውርዱ

ትምህርታዊ ምስሎች

ለተሻሻሉ የትምህርት ጥራት የተዘጋጀ የትምህርታዊ ቪዲዮዎች እና አጋዥ ስልጠናዎችን ይከታተሉ።

እዚህ ይመልከቱ

የመለማመጃ ጥያቄዎች

ለተለያዩ የትምህርት አይነቶች የሚያገልግሉ የጥያቄ መለማመጃ መልመጃዎችን እዚህ በማውረድ ይለማመዱ።

ጥያቄውን ያውርዱ

መሰረታዊ ፎርሞችንና ሰነዶችን

ትምህርታዊ ፎርሞች

መሰረታዊ የፍቃድ፣ ይምዝገባ ፎርሞችንና አስተዳደራዊ ቅሬታ መጠየቂያ ሰነዶችን ያግኙ።

ፎርሙን ይክፈቱ

የፖሊሲ ሰነዶች

የኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት ይፋዊ ፖሊሲዎች፣ የሥነ-ምግባር ኮድ እና ሌሎች አስፈላጊ የህግ ሰነዶች።

ሰነዱን ይመልከቱ

የስርዓተ-ትምህርቱ መመሪያዎች

ኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት በዝርዝር ያስቀመጣቸው ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ላሉ ትምህርቶች የተቀረጹ የስርዓተ ትምህርቱ መመሪያዎችን ይመልከቱ።

መመሪያዎችን ይመልከቱ

አዳዲስ መረጃዎች

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የብጹዕ አቡነ ሄኖክ ጉብኝት

መስከረም 15, 2018 ዓ.ም ኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤትን መርቀው ሲከፍቱ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሄኖክ ሳሪስ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ገዳም በመገኘት የኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት በቡራኬ ከከፈቱ በኃላ የትውልድ ግንባታው በሁለቱም ዘርፍ የተሳለ ትውልድ መፍጠር እንዲገባ መክዕክት አስተላልፈዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ

የቀለም ቀን በኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት

መስከረም 7, , 2018 ዓ.ም ተማሪዎች በጋራ ሲያከብሩ

የቀለም ቀን በኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት ሲከበር የቀለም ቀንድ የሚባሉትን እባቶቻቸውን እና የትምህርትን አስፈላጊነት እንዲረዱ ይደረጋል።

ተጨማሪ ያንብቡ

የኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ኅብረት ቀን

ሕዳር 25, 2018 ዓ.ም በኅብረት እውቀታችን እናጋራ

ትምህርት ቤታችን የተማሪዎች ኅብረት ቀን ሲያከብር ተማሪዎች የተስተካከለ ማኅበረሰባዊ አንድነትና መተሳሰብ እንዲኖረቸው የውይይት መድረኮችን ያዘጋጃል።

ተጨማሪ ያንብቡ

ተጨማሪ መድረኮች

አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ድህረ ገጹን አዘውትረው ይጎብኙ።

ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ የኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤትን ባርከው ሥራ ሲያስጀምሩ

ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፥ የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እሑድ መስከረም ፲፩~፳፻፲፰ ዓ.ም በገዳማችን ቅጽረ ግቢ የተገነባውን የኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤትን ባርከው ሥራ አስጀምረዋል። በቆይታቸውም ትምህርት ቤቱን ተዘዋውረው በመጎብኘት የትምህርት ቤትን አስፈላጊነት ተጨማሪ የተጠናከሩ የልማት ሥራዎችም እንዲሠሩ አባታዊ መመሪያ የሰጡ ሲሆን ቤተ ክርስቲያንና ሀገርን የሚረከብ ትውልድ እንዲፈራበት ቡራኬ ሰጥተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ

የብጹዕ ሕርያቆስ አባታዊ ምክሮች

ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ የኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤትን ባርከው ሥራ ካስጀመሩ በኃላ ትምህርት ቤቱን ተዘዋውረው በመጎብኘት የትምህርት ቤትን አስፈላጊነት ተጨማሪ የተጠናከሩ የልማት ሥራዎችም እንዲሠሩ አባታዊ መመሪያ የሰጡ ሲሆን ቤተ ክርስቲያንና ሀገርን የሚረከብ ትውልድ እንዲፈራበት ቡራኬ ሰጥተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ

የዓመቱ ትምህርት መጀመሪያ ዕለት

የዓመቱ የትምህርት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ዛሬ ሰኞ መስከረም 5 የጳዝዮን አክስዮን ማኅበር የቦርድ አባላት፣ ወላጆችና፣ ተማሪዎች በተገኙበት ተከናውኗል።በዕለቱ መርሐ ግብሩ በገዳማችን ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም ቀሲስ ሰሎሞን ተካ አማካኝነት ጸሎትና ቡራኬ እንዲሁም አባታዊ ምክር ተሰጥቷል። በጳዝዮን አክስዮን ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ በሆኑት ዶ/ር ሱራፌል ልዑልሰገድ አማካኝነት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክትና ኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት የተመሠረተበትን ዓላማ፣ የትምህርት ሂደቱን መሠረታዊ ነጥቦችን ለወላጆችና ተማሪዎች አሳውቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ

ያግኙን

አድራሻ

ሳሪስ አቦ፣ አዲስ ኣበባ፣ ኢትዮጵያ

ስልክ ቁጥር

+251 96 011 8811

ኢሜል

info@hohitetibeb.edu.et

የሥራ ስዓት

ከሰኞ -አርብ 8:00 AM - 5:00 PM

ቅዳሜ : 9:00 AM - 1:00 PM

መልዕክትዎን ይላኩልን

በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

ኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት ማን ነው?

ኆኅተ ጥበብ ትምህርት ቤት "በጳዝዮን አክስዮን ማኅበር" አማካኝነት በ2018 ዐ.ም የተመሠረተ ሲሆን የትምህርት አሰጣጥ ብቃትን ከሥነ ምግባር ጋር በማቀናጀት የትምህርት አገልግሎት ለመስጠት ተመሠረተ።

የተማሪና የመምህራን ምጥጥን ምን ያህል ነው?

ለእያንዳንዱ ተማሪ የግል ትኩረት ለመስጠት በአንደኛ ደረጃ ክፍሎች 15፡1 እና በመካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 18፡1 ዝቅተኛ የተማሪ-ወደ-መምህር ጥምርታ አለን።

ልዩ ድጋፍ ወይም ነጻ የትምህርት እድል ትሰጣላችሁ?

አዎ፣ በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ልዩ ድጋፍ እና በብቃት ላይ የተመሰረተ ነጻ የትምህርት እድል እናቀርባለን። ማመልከቻዎች በየዓመቱ ይገመገማሉ፣ እና ውሳኔዎች የሚደረጉት በሚገኘው የገንዘብ ድጋፍ እና በአመልካቾች ብቃት ላይ በመመስረት ነው።

ከመደበኛ ትምህርት ውጭ ምን አይነት እንቅስቃሴዎች ይገኛሉ?

ልዩ ልዩ የስፖርት ቡድኖችን፣ የሙዚቃ ፕሮግራሞችን፣ የስነጥበብ ክለቦችን፣ ሮቦቲክስን፣ ውይይትን እና የማህበረሰብ አገልግሎትን የሚያበረታቱ ዝግጅቶችን ከትምህርት ውጭ እናቀርባለን። ዝግጅቶች እንደ ወቅቱ እና የተማሪዎች ፍላጎት ይለያያሉ።

ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች እንዴት ይደግፋሉ?

የተለያዩ የትምህርት ፍላጎቶች ካላቸው ተማሪዎች ጋር የሚሰራ ቁርጠኛ የትምህርት ድጋፍ ቡድን አለን። ሁሉም ተማሪዎች ስኬታማ እንዲሆኑ ለመርዳት የግል የትምህርት ዕቅዶችን፣ ማመቻቸቶችን እና ልዩ መመሪያዎችን እናቀርባለን።

የማመልከቻ ሂደቱ ምን ይመስላል?

የማመልከቻ ሂደቱ የማመልከቻ ቅጽ ማስገባት፣ የልደት ሰርትፍኬት ማቅረብ፣ እንዲሁም ከሌላ ትምህርት ቤት ከመጡን የመልቀቂያና መሸኛ ደብዳቤ ለትምህርት ቤቱ ማቅረብ የሚጠበቅ ሲሆን ማመልከቻዎችሁ በኆኅተ ጥበብ ተቀባይነት ይኖራቸዋል፣ ነገር ግን ለሚቀጥለው የትምህርት ዘመን እስከ ነሐሴ 28, 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲያመለክቱ እንመክራለን።